ሴቶች ምቹ ሁኔታ ቢፈጠሩላቸው በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ከታየው የመስክ ምልከታ መገንዘብ መቻሉን ክብርት ሁሪያ አሊ ገለፁ።

ዓለም-አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ያከናወኗቸውን ተግባራት ሴቶች ምቹ ሁኔታ ቢፈጠሩላቸው በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ከታየው የመስክ ምልከታ መገንዘብ መቻሉን በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ድኤታ የሆኑት ሁሪያ አሊ ገልፀዋል።

በመስክ ምልከታው ከታዩ ስራዎች መካከል የሸክላ ስራ፣ የቲማቲም፣ የሙዝና የስንዴ ምርቶች እና አረጋውያን በመደራጀት የሰሯቸው የእጅ ስራዎች እና ሌሎችም ይገኙበታል።

እነዚህ ስራዎች አረጋውያንን እና አካል ጉዳተኞችን ማካተቱ መልካም እንደሆነና የመንግስት ትኩረት አቅጣጫ ከሆነው አካታች ብልፅግና የማምጣት ስራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ክልሉ የቱሪዝም መዳረሻ እንደመሆኑ በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶች በሎጆች አከባቢ ቦታ ቢመቻችላቸው እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ምርቶቻቸውን እንዲያቀርቡ ቢደረግ የተሻለ ውጤታማ ማድረግ እንደሚቻል የቦታ፥ የግብዓት፥ የገበያ ትስስር ክልሉና ዞኑ በቅንጅት በመስራት ቢያመቻችላቸው ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ እንደሚቻል ገልፀዋል።

በጉብኝቱ እንደ ችግሮች ከተነሱት መካከል የመሠረ ልማት ፥ የመኖ አቅርቦት፥ የመሸጫ ቦታ እጦት ምክንያት ከአቅማቸው በታች እንዲሰሩ እንዳስገገዳቸውና ትርፋማነታቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን በመግለፅ ደቡብ ምዕራብ የእምቅ ሃብት ባለቤት እንደመሆኑ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅበትም አሳስበዋል።

የተነሱ ችግሮችን በመንግስትና በማህበረሰብ ተሳትፎ የሚፈቱና የመንግስት ዋነኛ ስራዎች በመሆናቸው ችግሮቹ ክልሉ ሊፈታቸው እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

 

Please follow and like us: