Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በአፋር፣ በሶማሌና ፣በኦሮሚያ ክልሎች የሚተገበር ተንቀሳቃሽ የህክምናና የስነምግብ ክሊኒክ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።
በኢትዮጵያ በኦሮሚያ፣ በአፋር ፣ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ 18 ወረዳዎች ተግባራዊ የሚደረግ ተንቀሳቃሽ የህክምናና የስነምግብ ክሊኒክ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

በዕለቱ መልዕክት ያሰተላለፉት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ የሆኑት ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለፁት ፕሮግራሙ አርብቶ አደርና ተደራሽ ባልሆኑ አካባቢዎች በሚገኙ ክልሎች 12 የጤና ተቋማት 4 ሆስፒታሎችን ጨምሮ የሚደግፍ እንደሚሆን ገልፀዋል። ፕሮጀክቱ በዋናነት የህፃናትን የምግብ ምጣኔ ለማስተካከልና በወሊድ ወቅት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰዋል። በተለይም እናቶች፣ ሴቶችና ህፃናት ከሚደርስባቸው ተደራራቢ ችግሮች መካከል አንዱ በሆነው የህክምናና የተመጣጣኝ ምግብ እጥረትን ለማቃለል እንደሚረዳ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም በሰዉ ሰራሽና ተፈጥሯዊ በሆኑ ምክንያቶች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በተጨማሪ ከጾታዊ እና ጾታን-መሠረት ያረጉ ጥቃት ሰለባዎችንም የሕክምና እንክብካቤ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ እንደሚሰጥ በዕለቱ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ በጌትስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍና በተባበሩት መንግስታት ስነ ህዝብ ፈንድ አማካይነት የተካሄደ ሲሆን በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስቴር ፣የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሦስቱ ክልሎች የሴቶችናማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
