3 ሺህ 367 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 367 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳምንቱ በተደረጉ ዘጠኝ በረራዎች የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆን ከተመላሾች መካከል 18 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ መጋቢት 3/ 2017 በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፤ በዚህም እስካሁን 15 ሺህ 684 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ ይገኛል፡፡

 

Please follow and like us: