ፍትሃዊ የሆነ የማህበራዊ አገልግሎትን ለዜጎች ለማዳረስ መንግስት የዲጂታል አሰራር ዝርጋታ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ተናገሩ።

ሚኒስትር ዴኤታዋ በ አይ ዲ ፎር አፍሪካ 2025(ID4Africa2025 ) ላይ ከተሳተፈውና ኢርነስት ኤንድ ዮንግ ከተሰኘ የቴክኖሎጂ ኡባንያ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ኩባንያው የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ በተለያዩ ሀገራት የሠራቸውን ስራዎች ተሞክሮ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቅርቧል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ድርጅቱ ይዞት የመጣው የዲጂታል አሰራር ተሞክሮ የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን መረጃ በትክክል ለመመዝገብና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አጋዥ መሆኑን አንስተዋል።

ፍትሃዊ የሆነ የማህበራዊ አገልግሎትን ለዜጎች ለማዳረስ የኢትዮጵያ መንግስት የዲጂታል አሰራር ዝርጋታ ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ በዘርፉ ከተሰማሩ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራትና ተሞክሮዎችን መቅሰም እንፈልጋለን ብለዋል። የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚዎች መመዝገቢያ ስርዓት እንደ ሀገር ወጥና ትክክለኛ መረጃ እንዲኖር፣ ድግግሞሽን በማስቀረት እኩል የሃብት ክፍፍል እንዲኖር እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማስፈን ፋይዳው የጎላ ነው

Please follow and like us: