Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
3 ሺህ 521 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 521 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 3451 ወንዶች፣ 55 ሴቶች እና15 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 45 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3 ቀኝ 2017 ጀምሮ ስራው በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፤ በዚህም እስካሁን 39 ሺህ 397 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
Please follow and like us:
