Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት የቋሚና ቀጥታ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጎልበት ለማህበራዊ ሰራተኞች( social worker) ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል።
በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ መመሪያ ውስጥ የተካተቱት አጠቃላይ ፅንስ ሐሳቦችና የትግበራ ሰርዓቶችን በሚገባ በመገንዘብ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለማሳለፍ የሚችሉበትን አቅም በመገንባት የአገልግሎት አሰጣጣቸው ጥራትና ቅልጥፍና ኖሮት የፕሮጀክቱ ዓላማ እንዲሳካ ተቋማዊ ሐይል ለመፍጠር እንዲቻል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞች ና ወረዳዎች ለተወጣጡ ማህበራዊ ሰራተኞች (social workers) ስልጠና ተሰጠ።

በመድረኩ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ጥበቃ ማስተባበሪያ ና መከታተያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሹመቴ እንደገለፁት መንግስት ኖሯቸውን በከተሞች ያደረጉና በማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ ደሀና ተጋላጭ ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከድህነት ወጥተው ራሳቸውን ከመቻል ባሻገር በአገር ግንባታ ሒደት ውስጥ የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ከፍ ለማድረግ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰዋል። በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ለዜጎች የሚሰጡ የማህበራዊ አገልግሎቶች የተጠቃሚዎችን መብት ደህንነትና ክብር የሚጠብቁና ለጉዳትም የማያጋልጡ አሰራሮችን በመዘርጋት በእውቀትና ክህሎት መስራት እንደሚገባ ለስልጠና ተሳታፊዎቹ አስገንዝበዋል።

በስልጠና መድረኩ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የጉዳይ አያያዝ ኬዝ ኮንፍረንስ ምርጥ ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት የተደረገበተ ሲሆን የፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ ማንዋል ባስቀመጠው መሰረት ለተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የተሰጣቸውን ተቋማዊ ሀላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡ የስልጠና ተሳታፊ ባለሙያዎቹ ቃል ገብተዋል።
