ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከተማ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ መመሪያዎች ሌሎች ተያያዥ ሰነዶች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ለመጡ የስራ ክፍል ሃላፊዎችና ፈፃሚ ባለሙያዎች ማስፈፀሚያ መመሪያው ውስጥ የተካተቱ አጠቃላይ ፅንሰ ሃሳቦችንና የትግበራ ስርዓቶችና ሌሎች ተያያዥ ሰነዶች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ውሎና አዳራቸውን በከተማ ጎዳኖች ላይ ያደረጉ ዜጎችን በልዩ ድጋፍ አገልግሎት ዘርፍ በማካተት የገንዘብና የመሠረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራውን ዘርፍ የማስተባበርና የመምራቱን ሃላፊነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ወስዶ እያከናወነ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የከተማ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ቋሚ የመኖሪያ አድራሻ ያላቸውንና ሌሎች የልዬታ መስፈርቶችን አሟልተው የደሃ ደሃ ተብለው የተለዩትን በቋሚ ቀጥታ ድጋፍ ዘርፍ ይደግፋል።

በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች በማስተባበር የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ከሚያገኙት ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በማህበራዊ ሰራተኞች አማካኝነት በሚደረግ የቤት ለቤት ጉብኝትና ኬዝ ማኔጅመንት የመሠረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት ፍላጎት መግለጫ መረጃዎች በመታገዝ የገንዘብ፣ የእህል እና የአይነት ድጋፎችን በመስጠት በርካቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ መንግስት ኑሯቸውን በሃገራችን ከተሞች ላይ ያደረጉና መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት የፍትህ፣ የገንዘብ፣ የጉልበት ወይም የጤና ሁኔታ የገደባቸውና በማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ አካቶ በመሰራት ላይ ይገኛል።

በዚህም ደሃና ተጋላጭ ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከድህነት እንዲወጡ እና ራሳቸውን ከመቻል በዘለለ በሃገር ግንባታ ሂደት የሚኖራቸውን አስተዋፅኦ ከፍ ለማድረግ ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ስለ ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉ ገፆቻችንን ይጎብኙ

 

Please follow and like us: