Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴሩ ለአካል ጉዳተኞች የተሃድሶ ማዕከላት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ
የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ለአርባ ምንጭና ደሴ የአካል ጉዳተኞች የተሃድሶ ማዕከላት የሚያገለግሉ አጋዥ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደርጓል።

ድጋፉን የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ተወካይ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሲሳይ ጥላሁን ለማዕከላቱ የስራ ሃላፊዎች/ተወካዮች ባስረከቡበት ወቅት እንደተገለፁት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ አጋር አካላትን በማስተባበር የእንቅስቃሴ እክል የገጠማቸውን ወገኖችን ለመደገፍ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ለአርባ ምንጭና ደሴ የአካል ጉዳተኞች የተሃድሶ ማዕከላት የተደረገው ድጋፍም የጥረቱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። ድጋፉ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውና የእንቅስቃሴ እክል የገጠማቸውን ወገኖችን ችግር ለመቅረፍ የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅትም ልዩ ልዩ የአካል እክል ለገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ግልጋሎት መስጠት የሚያስችሉ ዊልቸሮች፣ ክራንቾች፣ የጆሮ ማዳመጫዎች፣ የብሬል ወረቀቶች፣ በትሮች፣ ዎከርስ፣ መቅረፀ-ድምፆች እና ሌሎችም አጋዥ ቁሳቁሶች መበርከቱን አስታውቀዋል። ሚኒስቴሩ በተለያዩ ጊዜያት መሠል ድጋፎችን ሲያደርግ መቆተዩንና ተግባሩ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በርክክቡ ወቅት ገልፀዋል።
Please follow and like us:
