የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የውጭ መረጃ አሰባሳቢ ልዑክ ጋር በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ተወያይቷል። በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልን አካታች ያደረገ የምርጫ ስርዓት እንዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሆነ ገልፀዋል ። በተለይም ሴቶች፣ ወጣቶች፣አካል ጉዳተኞችና ለችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከምርጫ ቦርድና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ከባለፈው ምርጫ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮችን በመውሰድ ለአሁኑ ደግሞ በቅድመ ምርጫ፣በምርጫ ወቅት እንዲሁም ድህረ ምርጫ ባሉት ሂደቶች ውስጥ ሴቶች፣ ወጣቶች አካል ጉዳተኞች ንቁ የምርጫ ተሳትፎን ከማድረግ በዘለል በመምረጥ፤በመመረጥና በታዛቢነት ሂደት ውስጥም እንዲሳተፉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ሚኒስትሯ ገልፀዋል። በተመድ የአፍሪካ ህብረት ቢሮ (UNOAU) የምርጫ ድጋፍ ክፍል ዋና ኦፊሰር አኪንየሚ ኦ. አዴግባላን በበኩላቸው ሚኒስቴሩ እየሠራ ያለውን ስራ አድንቀው ድርጅታቸው ምርጫው የተሳካና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በአቅም ግንባታ፣ በአካታች ህዝባዊ ተሣትፎ ንቅናቄዎች፣ የምክክርና የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የውጭ መረጃ አሰባሳቢ ልዑክ ጋር በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ተወያይቷል።

በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልን አካታች ያደረገ የምርጫ ስርዓት እንዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሆነ ገልፀዋል ።

በተለይም ሴቶች፣ ወጣቶች፣አካል ጉዳተኞችና ለችግር ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከምርጫ ቦርድና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከባለፈው ምርጫ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮችን በመውሰድ ለአሁኑ ደግሞ በቅድመ ምርጫ፣በምርጫ ወቅት እንዲሁም ድህረ ምርጫ ባሉት ሂደቶች ውስጥ ሴቶች፣ ወጣቶች አካል ጉዳተኞች ንቁ የምርጫ ተሳትፎን ከማድረግ በዘለል በመምረጥ፤በመመረጥና በታዛቢነት ሂደት ውስጥም እንዲሳተፉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

በተመድ የአፍሪካ ህብረት ቢሮ (UNOAU) የምርጫ ድጋፍ ክፍል ዋና ኦፊሰር አኪንየሚ ኦ. አዴግባላን በበኩላቸው ሚኒስቴሩ እየሠራ ያለውን ስራ አድንቀው ድርጅታቸው ምርጫው የተሳካና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በአቅም ግንባታ፣ በአካታች ህዝባዊ ተሣትፎ ንቅናቄዎች፣ የምክክርና የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል።

Please follow and like us: