የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባሉ ተግዳሮቶችና መፍትሔው ዙሪያ አጋር አካላትን ያሳተፈ የፓናል ውይይት ተካሄደ

‎’ሴት አመራሮች ለኢትዮጵያ ብልፅግና’ በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ በሳይንስ ሙዝየም ሲካሄድ የቆየው መድረክ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባሉ ተግዳሮቶችና መፍትሔው ዙሪያ አጋር አካላትን ያሳተፈ የፓናል ውይይት በማካሄድ ተጠናቋል።

በፓናሉ ውይይቱ በተለይ ‎ከፖሊሲ፣ ጥናትና ምርምር አንጻር በሚኒስትር መ/ቤቱ ሴቶችን አስመልክቶ የወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲተገበሩና በሁሉም አካላት ዘንድ ተፈፃሚ እንዲሆኑ በማደረግ እና በማረጋገጥ ረገድ የተሰሩ ስራዎች በሚኒስቴር መ/ቤቱ የፖሊሲ፣ ጥናትና ምርምር ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ትፍሲት ሰለሞን በሰፊው ተዳሰዋል፡፡
‎
‎ሴቶች በአመራርነትና በውሳኔ ሰጪነት ሂደት እንዲሁም በአስፈፃሚ ቦታዎች ላይ ሲሰሩ የሚያጋጥማቸው ተግዳሮቶች፣ ተግዳሮቱን እንዴት ማስተካከልና ማለፍ እንደሚቻል የቀጣዩ ትውልድ ሴት መሪዎችን ለማስተማር፣ ለመደገፍ እና ለማብቃት ምን አይነት ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባ ከተባበሩት መንግስታት ሴቶች ጉዳይ ድርጅት የተገኙት ፓናሊስት ደሴት አበበ አመላክተዋል፡፡
‎
‎ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በመከላከልና በማስወገድ እንደ ሀገር እና እንደ ተባበሩት መንግስታት ስነ ህዝብ ፈንድ የተሰሩ ስራዎችን፣ ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶች በተመለከተ የድርጅቱ ወካይ ቲኖስ ከበደ ማብራሪያዎች ሰጥተውበታል፡፡
‎
‎ከእናት ባንክ የመጡት ሌላኛዋ ፓናሊስት ትዕግስት አበበ በበኩላቸው የኢኮኖሚ አካታችነትና የሴቶች የፋይናንስ አካታችነት ለማረጋገጥ በፋይናንሰ ተቋማት በኩል የተወሰዱ እርምጃዎችን፣ በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶችንና ለሴቶች ምቹ በሆኑ የአሰራር ስርዓቶች ዙሪያ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡
‎
‎ክፍያ በማይከፈልባቸው ስራዎች የተሰማሩ ሴቶችን በተመለከት ያሉ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ተግባራዊ በማድረግ  ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ደግሞ ከኢትዮጵያ ሴቶች ጥምረት ወ/ሮ ሳባ ገብረመድህን አብራርተዋል፡፡
‎
‎የፓናል ውይይቱን ወ/ሮ የእልፍኝ አበጋዝ ከተባበሩት መንግስታት ሴቶች ጉዳይ ድርጅት የኢትዮጵያ አስተባባሪ የመሩት ሲሆን በርዕሰ ጉዳዮቹ ላይም ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም በክብርት ሚኒስትር  ኤርጎጌ ተስፋዬና ( ዶ/ር)በሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን አማካኝነት ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

Please follow and like us: