‎በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ‎500 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 500 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
‎ትላንት እና ዛሬ በተደረገ 2 ዙር በረራ የተመለሱት 108 ወንዶች፣ 373 ሴቶች እና 19 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 45 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ‎ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡ መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 1 ሺህ 546 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: