በየአካባቢው የአረጋውያን መንከባከቢያና የገቢ ማስገኛ ማዕከላት እንዲቋቋሙ ለማስቻል ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

በየአካባቢው የአረጋውያን መንከባከቢያና የገቢ ማስገኛ ማዕከላት እዲቋቋሙ ለማስቻል ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ጥሪ አቀረቡ።
‎‎ሚኒስትር ዴኤታዋ አለም አቀፉ የአረጋውያን ቀን አከባበር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሚኒስቴሩ የአረጋውያንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ሚናቸውን ለማጉላት የሚያግዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። በተለያዩ የክልል ከተሞች የአረጋውያን ማዕከላትን የመገንባትና የማስፋፋት ሥራዎች እየተሠሩ ቢሆንም፥ በሀገሪቱ ውስጥ ካለው የአረጋውያን ቁጥር አንፃር በቂ አለመሆኑን ተናግረዋል። ‎ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በየአካባቢው የአረጋውያን መንከባከቢያና የገቢ ማስገኛ ማዕከላት ለመገንባት መታቀዱን ገልፀው ስርዓት ሆኖ እንዲቀጥል በትኩረት መሠራት እንዳለበት አመላክተዋል።
‎የማዕከላቱ መገንባትና ገቢ የማመጨት ስራው እንዲጠናከር መደረጉ ለአረጋውያን የኢኮኖሚ ችግር መፍትሔ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ ማዕከላቱ አረጋውያን በእጆቻቸው ያሉ ልምድ፣ እውቀት እና ክህሎቶችን ወደ ቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፉባቸው ምቹ ስፍራ እንደሚሆኑም ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም ማዕከላቱ አረጋውያን እርስ በርስ የሚገናኙበት፣ የሚወያዩበት፣ ከአቻዎቻቸው ጋር መረጃ የሚለዋወጡበት እና ለአእምሮ ጤና ችግሮች እንዳይጋለጡ የሚጠበቁበት ይሆናሉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡
‎ በመሆኑም ክልሎች እና ባላድርሻ አካላት ይህንኑ ተፈጻሚ ለማድረግ ሚናቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዕለቱ ለአረጋውያን ተጠቃሚነት የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጥቷል።
‎

Please follow and like us: