ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ ትብብርና አጋርነትን ከአገራዊ አጀንዳዎች ጋር ያጣጣመና ሀገር በቀል የሀብት ማሰባሰብ ስልቶች ላይ ያተኮረ ነው- ክብርት ሁሪያ አሊ

‎በቅርቡ በተደረገው ‘ማህበራዊ ጥበቃ ለዘላቂ ልማትና ደህንነት’ በሚል መሪ ሃሳብ በማህበራዊ ጥበቃ ዘርፍ የተሰማሩ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች የተሳተፉበት ውይይት በመዲናችን መካሄዱ ይታወሳል።
‎በውይይት ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ፥ ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ ትብብርና አጋርነትን ከአገራዊ አጀንዳዎች ጋር ያጣጣመ ሀገር በቀል የሀብት ማሰባሰብ ስልቶችን በመተግበር ላይ እንደሆነች ገልፀው የኢትዮጵያን ውጤታማ አለም ዓለም አቀፍ ድጋፎችን አገራዊ ባለቤትነትን ያረጋገጡና ዘላቂ ለውጥ የሚያመጡ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ‎ኢትዩጵያያ በዚህ ዘርፍ በለውጡ ማግስት ያስመዘገበችው ቁልፍ ስትራቴጂዎችን ከሀገራዊ ዕቅዶች ጋር ማጣጣም፣ ስልታዊ ፋይናንስን መጠቀም፣ የአካባቢ አቅምን መገንባት የሚያስችል፣ ተጠያቂነትንና ግልፅነት ያለው የገንዘብ ድጋፍ ማረጋገጥን ያካትታል ብለዋል።
‎ሌሎች የአፍሪካ መንግስታት ግልጽ የሆነ አገራዊ ማዕቀፎችን እንዲያወጡ፣ ለአገራዊ ስርዓት ቅድሚያ እንዲሰጡ፣ የተቀናጀ ፋይናንስን ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ እና ግልፅነትን እንዲያሳድጉ ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል። አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶችና አጋር መንግስታትም የታክስ ማሻሻያዎችን እንዲደግፉ፣ ወጥ የልማት ትብብርን በፕሮግራም ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ የበጎ አድራጎት ካፒታልን ማሰባሰብ፣ አረንጓዴ/የአየር ንብረት ፋይናንስን ማሰባሰብ፣ በመረጃ ትንተና ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉና እና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን እንዲሁም የአየር ንብረትን የሚያስጠብቅ የፋይናንስ ስርዓት እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል።

Please follow and like us: