Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴሩ ከ28ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የቁሳቁስ ድጋፍ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀበለ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ28ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሀገር ኢኮኖሚ ከሚያበረክተው የጎላ አስተዋጽኦ ባሻገር ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጡ ከሚገኙ ድርጅቶች መካከል ግንባር ቀደሙ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አሁን የተደረገው ድጋፍ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለሚገኙና ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን በተለይም ሴቶችንና ህፃናትን ለማገዝ ትልቅ አቅም እንደሚሆንና ይህንን ቁሳቁስምድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል። በተጨማሪም ድጋፉ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተቸገሩ ቤተሰቦችን፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን በመደገፍ ረገድ ትልቅ እገዛ እንደሚደርግ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለማ ያደቻ በበኩላቸው፤ ድጋፉ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን አስታውቀዋል። አየር መንገዱ ድጋፋን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። በድጋፍ ከተሰጡ እቃዎች መካከል አልባሳትን፣ ቦርሳዎችን፣ ጫማዎች፣ የወጥ ቤት እቃዎች እቃዎች፣ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ይገኙበታል፡፡
Please follow and like us:
