በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 301 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 301 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 11 ዙር በረራ የተመለሱት 1875 ወንዶችና 385 ሴቶች እንዲሁም 41 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 75 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ‎

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ‎መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 8 ሺህ 585 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎
‎

Please follow and like us: