የሴቶች ጉዳይ ላይ የሚመክር አለም አቀፍ የመሪዎች ጉባዔ በቤጀንግ ቻይና ተካሄደ

የተለያዩ አገራት መሪዎች የተሳተፉበት በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ የመሪዎች ጉባዔ በቤጂንግ ቻይና በቻይና ኮንቬንሽን ማዕከል ተካሄዷል፡፡ ይህ ዓለም አቀፍ ጉባዔ የተከፈተው በቻይናው ኘሬዚዳንት በክቡር ሺ ዢፒንግ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ የተከበሩ ወ/ሮ አሚናን መሀመድን ጨምሮ የተለያዩ አገራት መሪዎችም በጉባዔው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ በኩል በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጐጌ ተስፋዬ የተመራ ልኡካን ቡድን ተሳትፎ ያደረገ ሲሆን ክብርት ሚኒስትር ኢትዮጵያ የቤጂንግ  +30 ቃል ኪዳን በመፈጸም ረገድ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን መስራቷን በዝርዝር አንስተዋል::  በተጨማሪም ጉባዔው የሴቶችን መብት ጥበቃ የበለጠ ለማጎልበትና ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም ተጨባጭ ተደማሪ ውጤቶችን ለማምጣት ትልቅ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ ዓለም አቀፍ ተቋማትና የቻይና መንግስትም በዚህ ረገድ እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Please follow and like us: