Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴሩ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሚውሉ ቦርሳዎችን ድጋፍ አደረገ::
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፍቅር የአእምሮ ውስንነትና እድገት ብሄራዊ ማህበርና የኢትጵያ መስማት የተሳናቸው ብሄራዊ ማህበር በተለያዩ ትምህርት ቤት ለሚያስተምሯቸው ህጻናት የተማሪዎች ቦርሳ ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፉ ወቅት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለፁት ድጋፉ የአእምሮ ዕድገት ውስንነትና መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎችን ማገዝ የሚጀመረው ከመረዳት ነዉና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለሀገር ኢኮኖሚ እስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ መደገፍ እንደሚገባው ጠቁመዋል። በተጨማሪም ተማሪዎቹ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶችን መሆናቸውን በማንሳት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ የሚያስችል ሲሆን ሚኒስቴሩ አሁንም ለማህበራቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። በተጨማሪም ፍቅር ኢትዮጵያ ማዕከልን ጎብኝተዋል።
Please follow and like us:
