Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
መንግስት ”ባለፈው ዓመት ለሴፍቲኔት 60 ቢሊየን ብር ድጎማ አድርጓል -ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር)
በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያት ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን በማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለማድረግ መንግሥት የተለያዩ የፖሊሲ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።
የገጠርና የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምን ጨምሮ የትምህርት ቤት ምገባ፣ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህንና ሌሎች ፕሮግራሞች ተቀርፀው በመተግበር ላይ መሆናቸው በማሳያነት የሚጠቀሱ ናቸው። በሴፍቲኔት ፕሮግራሞች ተጋላጭ የሆኑ በርካታ የህብረተስብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ በዘላቂነት ከተረጂነት እንዲላቀቁ እና ወደ ምርታማነት እንዲሸጋገሩ እየተሰራ ባለው ስራ አበረታች ውጤት መመዝገብ ችሏል። የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራሙን በራስ አቅም ለማስቀጠል መንግስት ሰፊ ስራ እየሰራና በቢሊዮን የሚቆጠር የበጀት ድጎማ እያደረገ ይገኛል።
”ባለፈው ዓመት ለሴፍቲኔት 60 ቢሊየን ብር፣ ለማዳበሪያ 84 ቢሊየን ብር፣ ለነዳጅ 140 ቢሊየን ብር ድጎማ መደረጉን ገልጸው፤ ዘንድሮ ለደመወዝ 160 ቢሊየን ብር ጨምረናል፤ በአጠቃላይ 440 ቢሊየን ብር ገዳማ ለድጎማ አውጥተናል” ብለዋል።
Please follow and like us:
