Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በኢትዮጵያ ለ20ኛ ጊዜ በሚከበረው ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀናት የንቅናቄ መርሐግብር ላይ ከሚዲያ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ
በኢትዮጵያ ለ20ኛ ጊዜ በሚከበረው ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀናት የንቅናቄ መርሐግብር ላይ ከሚዲያ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ላይ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት ጥበቃና ምላሽ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘካርያስ ደሳለኝ የዘንድሮ በዓል የሚከበረው “ፆታዊ ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል መሆኑን ገልፀዋል። ጥቃትን ያለመታገስ የንቅናቄ መርሐግብሩ ከህዳር 16 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
የውይይቱ ዋና ዓላማ የሚዲያ አካላት ለማህበረሰቡ ግንዛቤን በመፍጠር እንደሀገር ጥቃትን ለመከላከልና ለተጎጂዎች የተቀናጀ ምላሽ ለመስጠት የሚካሄደው የንቅናቄ መርሐግብር ስኬታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ እና ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።
Please follow and like us:
