Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በአንደኛ ሩብ አመት የመሠረታዊ ማሕበራዊ አገልግሎቶች ትስስር ያገኙ ሰዎች ከ466 ሺህ በላይ መድረሳቸው ተገለጸ፡፡
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በሁለተኛው ዙር ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የወረዳ የገጠር ሴፍቲኔት የማህበራዊ ባለሙያዎች መልዕክት ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ክብርት ሁሪያ እንደገለፁት የመሠረታዊ አገልግሎቶች ትስስር ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን በተለይም የቀጥታ ድጋፍ ለሚደረግላቸው የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ይህ አገልግሎት እጅግ አስፈላጊና ከተደራራቢ ችግር የሚታደጋቸው አገልግሎት እንደሆነ ገልጸዋል። አገልግሎቱ በየአካባቢው የሚገኙና በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት እንዲሁም በግለሰቦች ጭምር የሚደረጉ የጤና፣ የትምህርት፣ የቤት ግንባታና እድሳት፣ የምግብ፣ የገንዘብ እና ሌሎችም አይነት ድጋፎችን በፕሮጀክቱ ከታቀፉ ተጠቃሚዎች ጋር በማገናኘት ላለባቸው ተደራራቢ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡ እነዚህን አገልግሎቶች በማስተሳሰር በአንደኛ ሩብ አመት የመሠረታዊ አገልግሎቶች ትስስር ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚሰጥ አገልግሎት ያገኙ ሰዎች ከ466,407 ሺህ በላይ መድረሳቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ባለሙያዎቹ ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ እነዚህን ዜጎች ድጋፍና ክብካቤ ከማድረግ በዘለል በዘላቂነት እራሳቸውን ማቋቋም እንዲችሉና መንግስት ለጀመረው የብልጽግና ጉዞ የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የማህበራዊ አገልግሎቶች ዋና ዋና የድጋፍ አይነቶች የምግብ ድጋፍ፣ የመጠለያ ግንባታና እድሳት፣ የስነልቦና ድጋፍ፣ የመረጃና ግንዛቤ ድጋፍ ፣የነጻ ትራንስፖርት፣ የህጻናት እንክብካቤ ድጋፎች፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ የጤና አገልግሎቶች ድጋፍ፣ የትምህርት ድጋፍ፣ የህግ ድጋፍ፣ የግብርና አገልግሎቶች ድጋፍ በዋነኛነት ይገለጻል፡፡
