በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 406 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 406 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 11 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 959 ወንዶችና 407 ሴቶች እንዲሁም 40 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 56 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 18 ሺህ 224 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎
‎

Please follow and like us: