Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት ሴቶች( un women) የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይና የዩኤን ዊመን የኢትዮጵያ ከሆኑት ዶሪስ ምፑሙ ጋር የሴቶች ኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ በቅንጅት መስራት ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በውይይቱ ሚኒስትሯ እንደገለጹት ሴቶች በኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማጠናከር ከሚያግዙት ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የሴቶች የኢኮኖሚ አቅም ማጎልበት ስትራቴጂ ሰነድ በቅርቡ በይፋ ተመርቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የገለጹ ሲሆን ይህም አሁን ላይ በሴቶች ልማት ህብረት፣ ሴቶች በግብርና ኢኒሼቲቮችን አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የሴቶች፣ ሰላም እና ደህንነት (WPS) ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር (NAP) ማስጀመሪያ እቅድ ዙሪያ ፣ በጋራ ሀብት በማሰባሰብ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሚኒስቴሩ ለሚያደርገው ጥረት ድርጅቱ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ሴቶች( un women) የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይና የዩኤን ዊመን የኢትዮጵያ ከሆኑት ዶሪስ ምፑሙ በበኩላቸው በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀው ድርጅቱም ይህንን ለመደገፍ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Please follow and like us:
