‎ባለፉት አምስት ምዕራፍ የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ትግበራ በገንዘብ ድጋፍና በመሰረታዊ የማህበራዊ አገልግሎቶች ትስስር የመፍጠር ስራ ተሰርቷል

ለገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ውጤታማነት የሚያግዝ 3ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

‎‎የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማሕበራዊ ጥበቃ፣ ማስተባበርያ እና መከታተያ ተጠባባቂ ስራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ጀማል ባለፉት አምስት ምዕራፍ የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት የፕሮግራሙ ትግበራ አመታትም በገንዘብ ድጋፍና በመሰረታዊ የማህበራዊ አገልግሎቶች ትስስር መፍጠር ረገድ መጠነ ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀጸዋል። በቀጣይም ፕሮግራም ውጤታማ በማድረግ በራስ አቅም ለማስቀጠልና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብዙ መስራት ይጠበቃል ብለዋል። ስልጠናውም ዘርፉን በእውቀት ለመምራት የሚያስችል አቅም ለመገንባት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ‎ሰልጣኞች የያገኙትን ግንዛቤ ተግባራዊ እንዲያደርጉና እስከታች ካለው መዋቅር ጋር በቅንጅት እና በትብብር እንዲሰሩ መልዕታቸውን አስተላልፈዋል።

‎‎ስልጠናው መሠረታዊ የማህበራዊ አገልግሎት ትስስርን በማጠናከር፣ በጉዳይ አያያዝ ዙሪያ ባሉ የአሰራር ማዕቀፎች እና የማህበራዊና አገልግሎት ድጋፍ ፍኖተካርታ እና ነጻ ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ‎ላይ ያተኮረ ነው። ‎በሶስተኛው ዙር የስልጠና መርሐግብር ላይ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ከሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከክልል እና ወረዳ ከግብርና፣ ከጤና እና የማህበራዊ ዘርፍ የገጠር ልማታዊ ሴፍትኔት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል

Please follow and like us: