‎የሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ አቅርቦትን ለማሳደግ፣ አቅምን ባገናዘበ እና ደረጃው በጠበቀ መልኩ ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ዙሪያ የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመቅረፍ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት፣ በታዩ ለውጦችና ባጋጠሙ ችግሮች ላይ 3ኛው ዙር መደበኛ የብሔራዊ አብይ ኮሚቴ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

‎በውይይት መድረኩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለፁት የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦትና ተደራሽነትን የሚያረጋግጡ የፖሊሲ ትብብርና የቁጥጥር የስትራቴጂ ለውጦች እንዲደረጉ ለማስቻል በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀረፀው ፕሮግራም ውጤታማ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ለማህበረሰቡ ሰለ ንፅህና መጠበቂያና የወር አበባ ግንዛቤ እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል። መንግስት ምርቱ በአነስተኛ ቀረጥ ከውጭ እንዲገባና በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ አበረታች እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ‎በተጨማሪም ምርቱ በሀገር ውስጥ አምራቾች እንዲመረት እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋና የተጠቃሚዎችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን ለማሰቻል በስታንዳርድ መመራት ያስፈልጋል፤ የተጀመሩ  ብለዋል።

‎‎አብይ ኮሚቴው አባላት ከተቋማቸው ተልዕኮ አንፃር በሕግ ቁጥጥር፣ በፋይናንስ፣ በስርጭት አውታሮች እንዲሁም በግንዛቤ እና በግንኙነት ሂደት ውስጥ ያሉትን
‎መሰናክሎች በመለየት መፍትሄዎችን ለማበጀት እያደረጉት ላለው አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል። ‎እንደሀገር አቅርቦትን ለማሳደግ፣ አቅምን ባገናዘበ እና ደረጃው በጠበቀ መልኩ ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። በፈረንሳይ የልማት ድርጅት የተቀረፀውና ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።
‎

Please follow and like us: