Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሄልፕኤጅ ከአለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት ወደ ሀገር በቀል መሸጋገሩ በራስ አቅም የውስጥ ችግሮቻችንን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ፡፡
ሄልፕኤጅ ኢንተርናሽናል ወደ ሄልፕኤጅ ኢትዮጵያ ወደ ሀገር በቀል የተራድኦ ድርጅት መሸጋገሩን ተከትሎ ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለጽት፣ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓቶችን ለማጠናከር፣ አረጋውያንን ለመንከባከብና ለመጠበቅ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ሙሉ ተሳትፎቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን እነዚህን ግቦች ብቻውን ማሳካት እንደማይችል ገልጸዋል፡፡ ሄልፕኤጅ ከአለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት ወደ ሀገር በቀል መሸጋገሩ በራስ አቅም የውስጥ ችግሮቻችንን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ፡፡ ሄልፕኤጅ ኢንተርናሽናል ወደ ሄልፕኤጅ ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የተራድኦ ድርጅት መሸጋገሩን ተከትሎ ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለጽት፣ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓቶችን ለማጠናከር፣ አረጋውያንን ለመንከባከብና ለመጠበቅ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ሙሉ ተሳትፎቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን እነዚህን ግቦች ብቻውን ማሳካት እንደማይችል ገልጸዋል።
ሄልፕኤጅ ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት ወደ ሀገር በቀል መሸጋገሩ የቴክኒካል እውቀቶች፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና የአረጋውያንን የኑሮ ሁኔታ በጥልቀት በመረዳት አገራዊ ጥረቶችን በእጅጉ ያሻሽላል ሲሉ ገልጸዋል። ድርጅቱ ወደ ሀገር በቀል መሸጋገሩ አካባቢዊ ተቋማትን ከመገንባት ባሻገር ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍን ጠቁመዋል፡፡ ሄልፕኤጅ ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት ወደ ሀገር በቀል መሸጋገሩ የቴክኒካል እውቀቶች፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና የአረጋውያንን የኑሮ ሁኔታ በጥልቀት በመረዳት አገራዊ ጥረቶችን በእጅጉ ያሻሽላል ሲሉ ገልጸዋል።
ይህም ከለውጡ ሰው ተኮር በሆኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ሕይወት ለመቀየር በትኩረት እየተሰራ ያለውን የመንግስት ጥረት ያግዛል ብለዋል። ድርጅቱ ወደ ሀገር በቀል መሸጋገሩ ይህን ጅማሮ ከማጠናከር አልፎ አካባቢዊ ተቋማትን ከመገንባት ባሻገር ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍን ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም የሴቶች እና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሄልፕኤጅ ኢትዮጵያ ጋር በቅርበት መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጣለሁ ብለዋል።
