የህጻናት መብቶች እንዲከበሩ እና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የክልሉ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ ገለጹ

የህጻናት መብቶች እንዲከበሩ እና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የክልሉ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ ገለጹ።

‎‎በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “የህጻናት ጥበቃ እና የመጫወት መብት ለሁሉም ህጻናት” በሚል መሪ ቃል ዓለም ዓቀፉ የህጻናት ቀን የማጠቃለያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የህፃናት የእግርኳስ ውድድር ተካሄዷል። ‎የክልሉ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ፣ ባለፉት ዓመታት የህጻናት የመብት ጥሰቶች እና የጉልበት ብዝበዛ ለመከላከል በተደረጉ ጥረቶች የተገኙ አበረታች ለውጦች ማጠናከር ይገባል ብለዋል። የህጻናት መብቶች እንዲከበሩ እና ልዩ ጠበቃ ተደርጎላቸው ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

‎‎ቢሮው የህጻናት መብቶች እንዲከበሩ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከማሣደግ ባለፈ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ለሚሹ ህጻናት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን አንስተዋል። በመንግሥት እና በግል ተቋማት የተጀመሩ የህጻናት ማቆያ ማዕከላትን የማስፋፋት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አንስተው፤ የመጫወቻ እና የመዝናኛ ቦታዎችን ማስፋፋት ይገባል ብለዋል። ‎የክልሉ የህጻናት ፓርላማ አፈ ጉባኤ ፋህሌን አብዱራህማን፣ የህጻናት መብታቸው እንዲከበር እና ታሪክን አውቀው በአግባቡ እንዲያድጉ ሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ገልጿል።

‎‎ስለህጻናት መብት እየተሠራ ያለው የግንዛቤ ፈጠራ ከማሳደግ ባለፈ ድጋፍ ለሚሹ ህጻናት እንክብካቤ ማድረግ ይገባል ብሏል። የዘንድሮው የህጻናት ቀን የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ36ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ መከበሩን የ‎ክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል። ‎

Please follow and like us: