Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመንግስት ተቋማት ዘርፍ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የምስጋናና የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ጉልህ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላትና ተቋማት የምስጋናና የእውቅና መርሐግብር አዘጋጅቷል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከሚኒስቴሩ ጋር ማህበረሰቡን በተለይም ሴቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ፕሮጀክቶች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። ፕሮጀክቶቹ በመንግስትና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከርና በጋራ አብሮ መስራት ከተቻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ መሆናቸው ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ሴቶችን ብቻ ተሳታፊ በሚያደርገው የቅድሚያ ለሴቶች የ5ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የንቅናቄ ስራዎችን በጋራ ሲያካሂድ መቆየቱን በማስታወስ ሚኒስቴሩ ላሳየው አጋርነት እውቅና ተበርክቷል።
Please follow and like us:
