በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 083 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

‎በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 083 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 10 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 533 ወንዶችና 535 ሴቶች እንዲሁም 15 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 101 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 22 ሺህ 700 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
‎
‎

Please follow and like us: