ኢትዮጵያና ማሌዥያ በወጣቶች ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

‎የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤትና የማሌዥያ የወጣቶች ምክር ቤት የሁለትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
‎ከአፍሮ ማሌዥያ የወጣቶች ፎረም ምስረታ ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤትና የማሌዥያ ወጣቶች ምክር ቤት በጋራ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ‎ስምምነቱን የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፋአድ ገናና የማሌዥያ የወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሞሀድ ኢዛት አፊፊ ሃጅ አብዱል ሀሚድ ተፈራርመዋል።
‎‎ስምምነቱ በአቅም ግምባታ ስልጠና፣ በስራ ፈጠራ፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በንግድ፣ በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እንዲሁም በወጣቶች የልምድ ልውውጥና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራትን ያካተተ መሆኑን ምክር ቤቱ በማህበራዊ ገፁ አስተውቋል። በተጨማሪም የኢትዮ ማሌዥያ የወጣቶች ፎረምን ለማቋቋም የሁለቱ ተቋማት መሪዎች የተፈራረሙ ሲሆን ጥምር ፕሮጀክቶችኝ ለመንደፍና ለማስፈጸም ብሎም በኢትዮጵያና በማሌዥያ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በሳንይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ስራዎችኝ ለማከናወንም ከስምምነት ደርሰዋል።
‎

Please follow and like us: