ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት እንደሀገር ለሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ስኬታማነት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣና እንዲተባበር ጥሪ ቀረበ

ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት እንደሀገር ለሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ስኬታማነት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣና እንዲተባበር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሙና አህመድ ጥሪ አቀረቡ።

‎ጾታዊ ጥቃት በሴቶችና ህጻናትን ላይ ውስብስብ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ድርጊቱን ሁላችንም አጥብቀን ልናወግዘው ይገባል ብለዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን በቅንጅት እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። የንቅናቄ መርሐግብሩ ከህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ለማካሄድ የሚረዳ ሀገራዊ እቅድ ተዘጋጅቶ መግባባት መፈጠሩንና ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መገባቱን አስታውቀዋል። በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጥቃትን የማውገዝ፣ በጥቃት አስከፊነትና በመብቶቻቸው ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር፣ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት የተቀናጀ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማጠናከር፣

‎በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጡ ስትራቴጂዎችን፣ የአሰራር ማዕቀፎችን፣ መምሪያዎችና የቅብብሎሽ ስርዓቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል። እንዲሁም ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ የአንድ ማዕከልንና ጊዜያዊ ማረፊያዎችን ለማጠናከርና ተጎጂዎች አገግመው ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀል የሚያስችሉ ተግባራትን ለመደገፍ መታቀዱን ገልፀው እንደሀገር ለሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ስኬታማነት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣና እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።x

Please follow and like us: