Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ 500 የአካል ድጋፍ ቁሳቁሶችንና የ700 ሺህ ብር ድጋፍ ለክልሉ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ህብረት ተበረከተ።
አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀንን አስመልክቶ ሚኒስቴር መ/ቤቱና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ ያሰባሰብበናቸውን ዊልቸሮችን፣ ክራንቾችን፣ ሂሪንግ ኤይዶችን፣ ነጭ በትሮችን ሌሎች ቁሳቁሶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ግምታቸው ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ 500 የአካል ድጋፍ ቁሳቁሶችንና የ700 ሺህ ብር ድጋፍ ለትግራይ ክልሉ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት አበረከተ።

በዚሁ ዕለት የዕለቱ የክብር እንግዳ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች የሚኖሩበት አካባቢ በመሆኑ እነዚህን ዜጎች በህብረተሰቡ ውስጥ ለማካተት እና እኩል ተሳታፊ ለማድረግ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። አሁን ላይ በክልሉ ያለውን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም ይህንን በዓል ለማክበር በክልልሉ ለተገኙ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለፁት የአካል ጉዳተኞች ማህበራትን ከማጠናከር አኳያም በቅርቡ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መቐለ ከተማ በመገኘት ባደረገው ምልከታ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት የሚገኙበትን ሁኔታ በመመልከትና አስቸኳይ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በማመን በክልሉ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ህብረት በኩል ማህበራቱን መልሶ ለማቋቋምና ለማጠናከር ድጋፉ ይረዳል ሲሉ ገልፀዋል።

ቀደም ሲልም ሚኒሰቴር መ/ቤታችን ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ካሰባሰባቸው የተለያዩ የአካል ድጋፍ ቁሳቁሶች ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ተደራሽ ያደረገ ሲሆን የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞችን ቀን በማስመልከትም የተጀመረውን የፋይናንስ ፣ የቴክኒክና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው ዕለቱን ስናከብር ከዚህ በኃላ የአካል ጉዳትን በማይፈጥሩ አማራጮች ላይ በማተኮር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ውይይትንና ምክክርን ባህል በማድረግ ግጭትንና ጦርነትን ለማስቀረት ቃል መግባት አለብን ብለዋል። የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ ሂዳያ አሊ እንደገለፁት ግጭት እና ጦርነት አዳዲስ አካል ጉዳተኞችን ከመፍጠሩም ባሻገር ዋነኛ ሰለባ የሚያደርገው አካል ጉዳተኞችን በመሆኑ በዚህም ምክንያት እኛ አካል ጉዳተኞች በየትኛውም የሀገራችን አካባቢዎች የሀሳብ ልዩነቶች በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
