Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የትግራይ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ህብረት ህንፃ ለመስራት የሚያስችል የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
በ1000 ካሬ መሬት ላይ የሚገነባውና ሁሉን አቀፍ አገልግሎት መስጠት ያስችላል የተባለው የትግራይ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ህብረት ህንፃ ለመስራት የመሠረተ ድንጋዩን ተቀምጧል።

የመሠረተ ድንጋዩን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ሁሪያ አሊ፣የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንዲሁም የክልልና የኢትዮጲያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት አመራርና ተወካዮች በጋራ በመሆን ነው። በተጨማሪም ዕለቱን አስመልክቶ በመቐለ ከተማ የሚገኘውን የኦርቶፊዚዮቴራፒ ማዕከልና የአካል ድጋፍ ማምረቻና ተሃድሶ ማዕከልን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ክብርት ሁሪያ እንደገለፁት ማዕከሉ ችግሮችን የሚቋቋም እና ተግዳሮቶችንም ወደ እድል በመቀየር እየሠራ ያለውን ስራ አድንቀዋል።

መንግስት ለአካል ጉዳተኞች ተሃድሶ ማዕከላት እየሰጠ ያለውን ትኩረት ጠቅሰው ከዚህ አኳያም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከህንድ ኤምባሲና ጃይፐር ፉት ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበርና በቅንጅት በመስራት በአፋር ክልል ሎጊያ ሆስፒታል ለ260 አካል ጉዳተኞች የተሰጠው የአካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ተጠቃሽ ሲሆን ይህን አገልግሎት ወደ ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በማስፋትም ወንድ 151 ሴት 26 በድምሩ ለ177 አካል ጉዳተኞች የአካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት መስጠቱን አስታውሰዋል። በተጨማሪም ይህን መሠል ድጋፎችን የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላትን በማቀናጀት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ማዕከሉ ባለፉት 29 ዓመታት ውስጥ ከ200,000 በላይ አገልግሎቶችን መስጠቱን በጉብኝቱ ወቅት መረዳት ተችሏል ።
