ለተሟላ የህፃናት አስተዳደግና ለተሳካ ትውልድ ግንባታ የቅድመ ልጅነት ዘመን ልማት ፕሮግራም ላይ አትኩሮ መስራት እንደሚገባ ክብርት ሒክማ ከይረዲን ገለፁ

በቀደማይ ልጅነት እንክብካቤ ዙሪያ ስራዎችን ለማስጀመርና ለማጠናከር የሚያስችል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተካሂዷል።

‎‎በውይይቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሒክማ ከይረዲን፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ እንዲሁም ከተለያዩ ሴኬተር ቢሮዎች የተወጣጡ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። ‎ውይይቱም ወቅትም፥ የቀደማይ ልጅነት እንክብካቤ ልማት ፕሮግራም በአካልና በአእምሮ የዳበረ፣ በመልካም ስነምግባር የታነፀ፣ ጤናማና ብቁ ዜጋን ለማፍራትና ለህፃናት የወደፈት ሁለተናዊ እድገት ወሳኝ በመሆኑ ተግባራዊ ማድረግና ለትውልዱ የሚበጅ ደማቅ አሻራ ጥሎ ማለፍ እንደሚያስፈልግ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልፀዋል። የውይይቱ ዋና ዓላማም የቀዳማይ ልጅነት እድገትና ትምህርትን ማስፋፋት፣ የህፃናት የቀን ማቆያ ማዕከላትን፣ የህፃናት መዝናኛና መጫወቻ ስፍራዎችን ከልማት ስራዎች ጋር በማስተሳሰር ማስፋፋትና ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

‎‎በክልሉ የተጀመሩ ስራዎች አስተማሪ መሆናቸውን አድንቀው በቀጣይም ክልሉን ጨምሮ እንደ ሀገር ለተሟላ የህፃናት አስተዳደግና ለተሳካ ትውልድ ግንባታ ታስቦ የተቀረፀው ፕሮግራም የሚጨበጥ ውጤት እንዲያመጣ በየዘርፉ የበለጠ አትኩሮ መስራት እንደሚገባ ክብርት ሒክማ ከይረዲን አሳስበዋል።

‎የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ በበኩላቸው፥ በክልሉ ህፃናትን ማዕከል ያደርጉ በርካታ ተግባራት በየዘርፉ እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል። ‎በቀጣይም ከሴቶችና ማህበራዊ ሴክተር በተጨማሪ ከጤና፣ ትምህርት፣ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮዎች እና መሰል ባለድርሻ አካላት ታች ካለው መዋቅር ጋር በመቀናጀት፣ የእቅድ አካል በማድረግ፣ የማህበረሰቡን አቅም በማስተባበርና በባለቤትነት በማሳተፍ እና የክትትልና ግምገማ ስርዓትን በማጠናከር ለፕሮግራሙ ውጤታማነት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

Please follow and like us: