በቅድመ ልጅነት ዘመን እድገት እንክብካቤ አተገባበር ዙሪያ በጅግጅጋ ከተማ ምክክር ይካሄዳል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን በቅድመ ልጅነት ዘመን እድገት እንክብካቤ አተገባበር ዙሪያ ከሱማሌ ክልል የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር ለመምከር ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ሂክማ ከይረዲን ጅግጅጋ ከተማ ሲደርሱ የክልሉ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃሊማ ሀሰን አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Please follow and like us: