ፍልሰተኞችንና ከፍልሰት ተመላሽ ዜጎችን የሰብዓዊ ድጋፎችን ተደራሽ ማድረግ ላይ በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተሰፋዬ (ዶ/ር) የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ኃላፊ የሆኑትን ክብርት ጠይባ ሀሰንን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ።

ተቋማቱ ተደራሽ የሚያደርጓቸውን ፍልሰተኞችንና ከፍልሰት ተመላሽ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፎችን ተደራሽ ማድረግ በሚቻልበት ላይ በቅንጅትና በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል። በዚህም ሁለቱ ተቋማት በጋራ ከሚጋሯቸው ስልጣንና ተግባራት መካከል በሆነው ፍልሰተኞችንና ከፍልሰት ተመላሽ ዜጎችን የማህበራዊ አገልግሎት አሰጣጥ እና ደኅንነት ጥበቃ ሥራ በዘላቂነት ማጎልበት ላይም በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰዋል።

Please follow and like us: