Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብት ስምምነት ትግበራ በመፈጸም የተቋማት አፈጻጸም የተሻለ እንዲሆን የክትትል እና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል- ክብርት ሁሪያ አሊ
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለጹት የተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብት ስምምነት ትግበራን በመፈጸም የተቋማት አፈጻጸም በመንግስት ተቋማት ያለበትን ደረጃ በመፈተሸ የተቋማቱን አፈጻጸም በቀጣይነት እየተሻሻለ እንዲሄድ ለማስቻልና ቀጣይ የተጠያቂነት ስርዓትን ለማበጀት የሚያስችል የክትትል እና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
እነዚህ የክትትል እና ድጋፍ ስራዎች በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ባለድርሻ አካላትን በማካተት በየወቅቱ ሲከናወን መቆየቱን አስታውሰው የተጠቃለለ ሃገራዊ የአፈጻጸም ሪፖርት በማዘጋጀት ለ.ተ.መ.ድ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ወቅቱን ጠብቆ በማቅረብ ረገድ ያሉን መልካም ተሞክሮዎች አጠናክሮ ለመቀጠል ያግዛል ብለዋል፡፡ በሁሉም የመንግስት መዋቅሮች ውስጥ ኮንቬንሽኑ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን የቁጥጥርና የክትትል ስርዓት ለማጠናከር፣ የመረጃና የሪፖርት አያያዝ ለማሻሻል፤ የአፈፃፀም ደረጃን ለመለካት የሚያስችሉ ተግባራትን በላቀ ደረጃ ለማከናወን ከፌዴሬሽኑ እና ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት ጋር በቅርበትና በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ወደ ተለያዩ ክልሎች በመንቀሳቀስ የኮንቬንሽኑን አፈጻጸም መሰረት በማድረግ በተደረጉ ምልከታዎች ላይ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋትና የተለዩ ውሱንነቶችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመፍትሔ ሃሳቦችን የጋራ ማድረግ የሚቻልበትን አሳቻይ ሁኔታዎች በመጠቆም ውጤታማ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
