ሴቶች፣ ሕፃናትና ልዩ ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ከማንኛውም ጥቃትና መድሎ ተጠብቀው፣ ሰብዓዊ ክብራቸውና ህጋዊ መብታቸው ተከብሮ በእኩልነት መኖርና ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ በቅንጅች መስራት ይገባል

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመተባበር በኮሚሽኑ አቤቱታ አቀራረብና ማስተናገጃ ስርዓት ላይ ለሴቶችና ሕፃናት መዋቅር የግንዛቤ ማስጠበጫና የምክክር መርሐግብር አዘጋጅቷል።

‎‎በመርሐግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ክብርት ሁሪያ አሊ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞችና ሌሎች ልዩ ጥበቃና ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ከማንኛውም መድሎና ጥቃት ተጠብቀው፣ ሰብዓዊ ክብራቸውና ህጋዊ መብታቸው ተከብሮ በእኩልነት መኖርና ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ በቅንጅች መስራት ይገባል ብለዋል። ‎ሰብዓዊ መብቶች እርስ በእርስ የሚተሳሰሩና የሚደጋገፉ መሆናቸውን ጠቅሰው እንደ ዜጋ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች የተጎናፀፏቸው ሁለንተናዊ መብቶች ሳይሸራረፉ ሊተገበሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ከሴቶች፣ ሕፃናትና ልዩ ድጋፍ ከሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የአቤቱታ አቀባበልና የማስተናገጃ ስርዓት ላይ የአስፈፃሚ አካላትን አቅም ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎‎ለዚህም ሚኒስቴሩ ከኮሚሽኑና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው፥ ስልጠናው በጋራ መዘጋጀቱም የጥረቱ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። በኢሰመኮ የዋና ከሚሽነር ጽ/ቤት ሃላፊ ቃልኪዳን ደረጄ በበኩላቸው፥ ኮሚሽኑ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያንን የተመለከተ ክፍል በማቋቋም ለሰብዓዊ መብት መከበር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

Please follow and like us: