በቀጣይ ምርጫ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ሴቶች ንቁ ተሣትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሴቶች በአመራርነትና ውሳኔ ሰጪነት ዙሪያ ግንዛቤ እንዲያገኙ ከሁሉም ክልሎች ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮና ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለተወጣጡ የስርዐተ ፆታ ባለሙያዎች ሴቶች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

በዕለቱ በሚኒስቴሩ የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን እንደገለፁት ባለፉት አምስት አመታት ሴቶች ቀአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ቦታዎች የላቀ ተሳትፎ ያደረጉበት እንደነበር አስታውሰዋል። ነገር ግን ከኢትዮጵያ ሴቶች አኳያ አሁንም በቂ ባለመሆኑ ሴቶች በቀጣይ ምርጫ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ንቁ ተሣትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ሚኒስቴሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተተኪ ሴት አመራሮችን ለማፍራት ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ላሉ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። ከዚሁ ጎን ለጎንም ዘላቂና ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖር የሚያስችሉ ፖሊሲዎችና የህግ ማዕቀፎች በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ ሴቶች በሁሉም መስክ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ጥረቶችን እየተደረጉ እንዳሉም ተናግረዋል።

ለዚህም በተለይ የዩኒቨርሲቲ ሴት ምሁራን አመራሮች እንዲሁም የስርዓተ ፆታ ባለሙያዎች ያሉ ክፍተቶችን በምርምርና በጥናት እንዲሁም ግንዛቤ በመፍጠር ተተኪ ሴት አመራሮችን በአመራርነትና ውሳኔ ሰጪነት እንዲመጡ አጋዥ በመሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል። ሰልጣኞች በቆይታቸው በአመራር ታሪክ የሴቶች ተሳትፎ ፣ አመራርነትና ሴቶች ማህበራዊ ወግ ለውጥ (Social Norm)፣ የተቋማት መመዘኛ ማዕቀፍና መሰል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለ2 ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

Please follow and like us: