Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል – ክብርት ሁሪያ አሊ
አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን አከባበር መሳካት ጉልህ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ተቋማት የእውቅና እና የምስጋና መርሀ-ግብር ተካሂዷል።
የአለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀንን አስመልክቶ ተሞክሮዎችን እና የቀጣይ በአል አከባበር እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በዚሁ ጊዜ፥ ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በየዓመቱ ሲከበር ዋነኛ ግቡ የአካል ጉዳተኞችን ሰብአዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስገንዘብና ሁለንተናዊ ተሳትፎአቸውን ለማረጋገጥ እንደሆነ ተናግረዋል። በዚህ ረገድ በቅርቡ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተካሄደው የዘንድሮ የአካል ጉዳተኞች ቀን ከመታሰቢያነት ባለፈ ውጤታማ ስራዎች የተከናወነበትና ዓላማውን ያሳካ እንደነበረ አስታውቀዋል። በዓሉን ሞክንያት በማድረግ ለክልሉ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ህብረት ማጠናከሪያ የሚውል የ700 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል። ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ግምታቸው ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ 540 ልዩ ልዩ የአካል ድጋፍ ቁሳቁሶችን ለክልሉ ኦርቶ ፊዚዮቴራፒ ማዕከል ማስረከብ መቻሉን ጠቁመዋል። በተጨማሪም የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ ለሚገኙ ማህበራት ህብረት የሚሆን የህንፃ መስሪያ ቦታ መስጠቱና የመሰረተ ድንጋይ መጣሉን አስታውሰው ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ከአመት እስከ አመት ሊያሰራ የሚ
ችል እቅድ በማዘጋጀት፣ ቅንጅታዊ ስራን በማጠናከር፣ ሀብት በማሰባሰብ ተጨባጭ ውጤት ሊያመጣ የሚችል ተግባራት መከናወን እንዳለበት ተናግረዋል። ሁነቱ ለአንድ ቀን ብቻ በአዳራሽ ወስጥ ተከብሮ የሚያበቃ ሳይሆን የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በተጨባጭ እስኪረጋገጥ ድረስ የእለት ተእለት ተግባር ሆኖ ሊቀጥል፣ በጥናት ሊደገፍና ስትራቴጂ ተነድፎ መፈፀሞ ይኖርበታል ብለዋል።

የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ለአንድ ተቋም ብቻ የሚተው ሃላፊነት ሳይሆን ሁሉንም ይመለከታል ያሉት ክብርት ሁሪያ ሚኒስቴሩ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በቀጣይም የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ በበኩላቸው በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ያለውን የተዛባ አመለካከት በመቅረፍ መብቶቻቸውን እንዲያረጋግጡና የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
