‎ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው የሚለወጡበት ምቹ ሁኔታና የስራ ዕድል ለመፍጠር በቅንጅት መስራት እንዳሚገባ ክብርት ሁሪያ አሊ ገለፁ

ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን መከላከል፣ የሚያስከትለውንም ተፅዕኖ መቋቋም እና ለተጓጂዎች ምላሽ ለመስጠት ያለመ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

‎‎በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ፥ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት በዜጎችና በሀገርም ላይ የከፋ ጉዳት እያደረሰ ስለመሆኑ አንስተዋል። ‎ችግሩን ለመከላከልና ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀትም ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ‎ኢ-መደበኛ ፍልሰትን በመከላከል ደህንነቱ የተጠበቀና ህጋዊነት የተከተለ አካሄድን ከማበረታታ ባሻገር የፍልሰት ተጎጂዎች የማህበራዊና ስነልቦናዊ ድጋፍ እንዲያገኙና ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ‎ለስራም ሆነ ለተሻለ ኑሮ መንቀሳቀስ ተፈጥሯዊና ህጋዊ መሆኑ ገልፀው ግንዛቤ በማስጨበጥ ዜጎች መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት አመራጭ በመጓዝ ከሚደርስባቸው ጉዳት ለመታደግ ከቤተሰብ ጀምሮ ማህበረሰቡና ተቋማት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

‎በሌላ በኩል ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው የሚለወጡበት ምቹ ሁኔታና የስራ ዕድል ለመፍጠር በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል። ‎መንግስት እንደ ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ የመሳሰሉ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍ እየሰሩ ያሉ በጎ አድራጎት ተቋማትን ጥረት ያደንቃል፤ አስፈላጊውንም ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል።

Please follow and like us: