ጠንካራ የሆነ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት በመዘርጋት የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትን ዘላቂና በራስ አቅም ወደተገነባ ሂደት መቀየር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ይህ የተገለጸው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክትን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ጠንካራ የሆነ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት መዘርጋት ዜጎች የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማስቻል የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትን ዘላቂና በራስ አቅም ወደተገነባ ሂደት መቀየር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከሚያደርጋቸው የአቅም ግንባታ፣ የድጋፍና ክትትል ስራዎች በተጨማሪ ሴክተሩን ጨምሮ ስራው በቀጥታ ከሚመለከታቸው ፈፃሚ ተቋማት ጋር በመሆን ወቅቱን የጠበቀ የአፈፃፀም ግምገማ በማድረግ የትግበራ አቅምን መገምገም የታዩ መልካም ተሞክሮዎችን ለይቶ በማስፋትና ተግዳሮቶችን ደግሞ በማረም ትምህርት ለመውሰድ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

ዜጎችን በተሻለ ሁኔታ ለማገልገልና የፕሮግራሙን አፈፃፀም ስኬት ወደ ላቅ ደረጃ በማሸጋገር ማህበረሰብ አቀፍ ተሳትፎዎችን በማስፋፋት ለተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋዕኦ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Please follow and like us: