Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ፋይዳ ከኢኮኖሚና ማህበራዊ ጠቀሜታው ባለፈ ሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከልና ጥቃት ከደረሰም በኃላ ጥቃት አድራሾችን በቀላሉ ለመለየት አስቻይ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ተገለፀ
ይህ የተገለፀው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሴክተር ፣ አመራሮች እና ኃላፊዎች ለሴት አደረጃጀቶች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የምክክርና የንቅናቄ መድረክ ላይ ነው።

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በዕለቱ እንደገለፁት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የሴቶችና ህፃናትን ሁለንተናዊ መብት ማስፈፀሚያ መሳሪያ መሆኑን ገልፀው ከኢኮኖሚና ማህበራዊ ጠቀሜታው ባለፈ ደህንነታቸውን በማስጠበቅ ሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችል እንደሚሆን ገልፀዋል። ጥቃት ከደረሰም በኃላ ጥቃት አድራሾችን በቀላሉ ለመለየት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፍጠር ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህጻናት ደህንነታቸው ተጠብቆ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችንም እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል። በተጨማሪም ሴቶች በኢኮኖሚው እኩል ተሳትፎ በማድረግ ብድር ለማግኘት፣ በስራ ፈጠራ ላይ ላሉ ሴቶች እና መደበኛ ባልሆኑ ዘርፎች ለተሰማሩ ሴቶች ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ጠቁመው ይህም አካታች የሆነ የኢኮኖሚ ስርዐትን በመፍጠር የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ የሚያረጋግጥ ይሆናል ብለዋል።

አገልግሎቱ በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ በህብረተሰቡና በሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤና ንቅናቄ በመፍጠር፣ ያልተመዘገቡ ሴቶችን በልማት ህብረቶች በመለየት እንዲመዘገቡ ማስቻል፣ሴቶችና የህጻናት ምዝገባ ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግ፣ ከተሳታፊዎች እንደሚጠበቅና ለተግባራዊነቱም እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዮዳሄ አርአያስላሴ በበኩላቸው ዲጂታል መታወቂያ ከመታወቅም ባለፈ የስርዐተ ፆታ ልዩነቶችን በማጥበብ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንደሚቀርፍ ገልፀው በተለይም ከቤት ውስጥ የማይወጡ ብዙ እናቶችን በቤታቸው ሆነው የዲጂታል አገልግሎቶችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል። የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ብርቱካን ሲሳይ እንዳሉት፣ ፋይዳ የሴቶችን መብትና ደህንነት ለማረጋገጥ አስቻይ መሆኑን አመልክተዋል። በክልሉ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያን ወደ ትግበራና ምዝገባ ወቅቶች የገጠሙ ችግሮችንና ያሉ አስቻይ እንዲሁም ግልፅ ያልሆኑ ሂደቶች ላይ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶበታል።
