የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የቅድመ ልጅነት እንክብካቤና ዕድገትን በተቀናጀ አግባብ ለመፈፀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የቅድመ ልጅነት እንክብካቤና እድገት (ECD) በሁሉም የክልሉ ዞኖች፣ከተማ አስተዳዳሮች እና ወረዳዎች በተቀናጀ አግባብ ለመተግበር የሚያስችል የስምምነት ከዞንናና ከተማ አስተዳዳር ምክትል ከንቲባዎችና ምክትል አስተዳዳሪዎች ጋር ተፈራርመዋል፡፡

‎ስምምነቱን የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት መብት ጥበቃና ምላሽ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዘቢደር ቦጋለ በአፈራራሚነት፣ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤሊያስ ፣ የሚመለከታቸው ተፈራራሚ ሴክተሮች፣ምክትል ክንቲባዎችና ምክትል አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።‌‎ የመግባቢያ ስምምነቱ በክልል የጤና ፣የትምህርት እና የከተማ ልማት ቢሮዎች ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች የተፈራረሙ ሲሆን ይራውን በእቅድ የመምራትና በየጊዜው እየገመገሙና ክፍተቶችን የማራም ስራውን በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳዳር በአቶ አበባየሁ ታደሰ የሚመራና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ የሚያስተባባረው መሆኑ ተገልፃል፡፡

በተመሳሳይ በታችኛው የዞን፣የከተማ አስተዳዳር መዋቅር በምክትል ከንተቢና አስዳዳሪ እንዲመራና ተግባራዊ እንዲደረግ ስምምንቱን ተፈራርመው ተቀማት በተሰጣቸው ተግባርና ኃፊነት ጋር በማስተሳሰር የግልና የጋራ እቅዶችን በማዘጋጀት ወደተግባር የሚገባና በየጊዜው የሚገመገም እንደሆነና ተቋማትም በዚህ ተግባር የሚለኩበት ስርዓት እንደሚሆን ስምምነት ላይ ተደርሳል፡፡ ‎በአጠቃላይ ስምምነቱ የህፃናትን ጥበቃና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ የጤናና አመጋገብ ስርዓትን ለማጎልበት፣ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትን ለማጠናከር፣ የህፃናት ተስማሚ መሠረተ ልማትና መጫወቻ ቦታ ለማቋቋም፣ የማህበረሰብ ተሳትፎና ግንዛቤ ለማጠናከር እንዲሁም የአሰራር ሥርዓትና ቅንጅት ለማጠናከር እንዲረዳ ትብብርና ቅንጅትን በመፍጠር የተደራሽነት ወሰንን ለማሳደግና የአገልግልት ጥራትን ለማምጣት የነገ ሀገር ተረካቢ ተውልድን ለመቅረፅ ያለመ ነው። ‎

Please follow and like us: