Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ህጻናት ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት አጠቃቀም እንዲኖራቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊያበረክቱ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት አጠቃቀም (Safer Internet Day) ለሁለተኛ ጊዜ ሰራሽ አስተውሎት (AI)” እና ስማርት ቴክኖሎጂዎች ላይ በማተኮር ተከብሮ ውሏል፡፡
በዕለቱ በተደረገው የፓናል ውይይት ህፃናት በቴክኖሎጂው የሚያገኙትን እውቀት ያህል፣ በውስጡ ያሉትን አደጋዎችም መረዳት እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ህጻናት ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት አጠቃቀም እንዲኖራቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊያበረክቱ ይገባልም ተብሏል፡፡ ህጻናት እንደ ሳይበር ጥቃት (Cyberbullying) ፣ ከሐሰተኛ መረጃዎችና ከማንነት ስርቆት ራሳቸውን እንደዚሁም ሌሎችን ለመጠበቅ የህፃናት ፓርላማ አባላት፣ ግንባር ቀደም ሚና መወጣት እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡
በተጫማሪም የህፃናት ፓርላማ አባላት ሕፃናትን ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ከጉልበት ብዝበዛ መከላከል ላይ ድምፅ መሆን ፣ በትምህርት ጥራትና በሥነ-ተዋልዶ ጤና ግንዛቤ ላይ በስፋት መስራት እንዳለባቸው በመድረኩ ተገልጿል፡፡ በእለቱ የህፃናት ፓርላማ አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸው ስለ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ያላቸውን ግንዛቤ የቀየረና ወደፊት በመስኩ ለመሰማራት ያላቸውን ዝንባሌ ጠቁመዋል፡፡
Please follow and like us:
