Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሚያከናውናቸው ዘላቂና አስተማማኝ የማህበራዊ ጥበቃና ሰው ተኮር ስራዎች ላይ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ
ይህ የተገለፀው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) መንግስት የሁለቱን አገራት ሰብአዊ ትብብርና የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርለሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተምር ስጦታ አበርክቷል።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ለተደረገው ስጦታ አመስግነው በቀጣይ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሚያከናውናቸውን በዘላቂነት የዜጎችን ህይወት በሚቀይሩ የማህበራዊ ጥበቃና ሰው ተኮር ስራዎች ላይ በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል:: ይህ ስጦታ በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል ያለውን እየተጠናከረ የመጣ የዲፕሎማሲና የሰብአዊ አጋርነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰውትብብሩን በማሳደግና ማኅበራዊ ትስስርን በማጠናከር፣ ሁለቱ አገራት ጠንካራ፣ አቅሙ የዳበረ ማኅበረሰብ ለመገንባት ያላቸውን የጋራ ራዕይ የሚያንጸባርቅ መሆኑንም ጠቁመዋል። ስጦታውለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለበጎ አድራጎት ማህበራት በኩል የሚሰጥመሆኑንም ጠቅሰዋል።

በአዲስ አበባ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኤምባሲን በመወከል የተገኙት አቶ ናስር አህመድ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ወዳጅነት አረጋግጠዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያን የማህበራዊ ጥበቃና ሰው ተኮር ስራዎች ለሚሰሩ ስራዎችን ለመደገፍና በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል።
