በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የሴቶችን እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈረመ፡፡

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የካናዳው ኒያግራ ፎልስ ዩኒቨርሲቲ (UNF) እና ኢድ ኮኔክት ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የሴቶችን እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ ከተካተቱ ተግባራት መካከል በበይነ መረብ የሚሰጡ የሰርቲፊኬት ፕሮግራሞችን ለወጣቶች እና ለሴቶች ማዳረስ፣ በማህበራዊው ዘርፍ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና የውሳኔ አሰጣጥ ስልጠናዎችን መስጠት፣ ዓለም አቀፍ የትምህርት ጥራት እና ቴክኖሎጂ ተሞክሮችን  ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የሰው ኃይልን ማጎልበት ይገኙበታል፡፡

Please follow and like us: