Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ጋር በመተባበር በቀዳማይ ልጅነት እድገት ዙሪያ ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ የአስፈፃሚ አካላትን አቅም ለማጎልበት ስልጠና እየሰጠ ነው
በስልጠና መርሐ ግብሩ ከክልል ሴቶችና ማህበራዊ፣ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከከተማ ልማት ሴክተር ቢሮዎች የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የሚኒስቴሩ የህፃናት መብት ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዘቢደር ቦጋለ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የቀዳማይ ልጅነት ዘመን ለህጻናት የአእምሮ፣ የአካል፣ የስሜትና የማህበራዊ ዕድገት መሠረት የሚጣልበት ወሳኝ ዘመን መሆኑን ገልፀዋል። ለዚህም ብሔራዊ የቅድመ ልጅነት ዘመን እድገትና ትምህርት ፖሊሲ ማዕቀፍ መቀረጹንና ወደ ተጨባጭ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት የሚያስችል የማስፈፀሚያ ስትራቴጂክ ሰነዶችን በማዘጋጀት በስራ ላይ በመዋሉል ተግባሩ እንዲስፋፋና እንዲጠናከር በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የዛሬው መድረክ የህፃናት ሁለንተናዊ እድገትን በተመለከተ የሁሉም የመንግስት ተቀማትን፣ የማህበረሰብን፣ የአጋርና የተባባሪ አካላትን ቅንጅትና ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀው፡፡ ለዚህም በዋናነት የጤና፣ ትምህርት፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች በአግባቡ ተቀናጅተው፣ የጋራ ድርጊት መርሀ ግብር በመቅረፀ፣ የሰው ኃይልና በጀትን በመመደብ ወደትግበራ መገባት እንደሚገባ በአፅእኖት ተገልጿል፡፡
ለዚህም ለተግባር የሚያግዝ በዘርፉ ያሉ የአሰራር ማዕቀፎች ግንዛቤ የመፍጠር እና በተገኙ ተሞክሮዎች ዙሪያ ልምድ ለመለዋወጥ፣ ክፍተቶችን ለመሙላት ብሎም በቀጣይ ተግባራዊና ውጤታማ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ከበደ ወርቁ በበኩላቸው፥ ማዕከሉ በአዲስ አበባ እየተተገበረ ላለው የቅድመ ልጅነት ልማት ፕሮግራም አፈፃፀም ጉልህ አስተዋጽዖ እያበረከተ ሲሆን ማዕከሉ በአምስት ክልሎች የፖሊሲውን አተገበባር የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ለአስፈፃሚ አካላት ስልጠና የመስጠት ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተግባሩ ለእናቶች ጤናና ለህፃናት እድገት ወሳኝ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ እንዲሁም ተግባሩን ወደ ወደ ሌሎች ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቅንጅት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
