Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 2 ሺህ 9 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 9 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ባለፈው ሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆን ከተመላሾች መካከል 38 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 56 ሺህ 225 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
Please follow and like us:
