Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በዳውን ሲንድረም እና በአእምሮ ዖድገት ውስንነት ዙሪያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚስተዋሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው
ይህ የተገለፀው ፍቅር የኢትዮጵያ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ማህበር፣ ከኢፊዲሪ ሴቶችና ማህቀራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከስፔሻል ኦሎምፒክስ እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር ለ11ኛ ጊዜ “Together against Loneliness” “ብቸኝነትን በአንድነት እንመክት” በሚል ዓለም አቀፍ መሪ ቃል በተከበረበት ወቅት ነው ።
በዕለቱ የሚኒስቴሩ ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለፁት በዳውን ሲንድረም እና በአእምሮ ዕድገት ውስንነት ዙሪያ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚስተዋሉ የግንዛቤ ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ ሰፊ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። በተለይም የዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆችን የሚያሳድጉ ቤተሰቦች ከማህበረሰቡ የመገልና ያለመካተት ስሜትን እንዲያስተናግድ ይገደዳሉ ሲሉ ገልፀዋል። ዕለቱን በተለያዩ ሁነቶች ሲከበርም ዋና ዓላማው ማህበረሰቡ ስለ ዳውን ሲንድረም ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ በአዲስ እይታ እንዲተካ ለማድረግ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች እና ዜጎች ተገቢውን ትምህርት፣ ስልጠና እና ማህበራዊ ተሳትፎ እንዲያዳብሩ አስፈላጊው ድጋፍ ከተደረጋለቸው ለራሳቸውም ሆነ ለሀገራቸው ድንቅ ስራዎችን መሥራት እንደሚችሉ በተለያዩ ጊዚያት ማየት በመቻሉ በሁሉም መስክ ዘርፈ ብዙ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል።
