Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አካታች የሆነ የትምህርት ስርዐትንና ማህበራዊ መስተጋብርን የሚያስፋፉ ድርጅቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በደቦራ አካዳሚ አዲስ የተገነባውን የውጭ መጫወቻ ስፍራ መርቀው የከፈቱ ሲሆን፣ ስፍራው የበለጠ ሳቢና አካታች ማህበረሰብ ለመገንባት ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል ።
ሚኒስቴሩ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አካታች የሆነ የትምህርት ስርዐትንና ማህበራዊ መስተጋብርን የሚያስፋፉ ድርጅቶችን እንደሚደግፍ ገልፀው ድጋፍ ሰጪ የሆኑ ስፍራዎችን ማዘጋጀት ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚገባቸውን ጥበቃ እና እድል እንዲያገኙ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰዋል። የመጫወቻ ሜዳው ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የኢትዮጵያ ህፃናት ትምህርት የመደገፍ መርሃ ግብር አካል ሲሆን ህፃናቱ ከአካዳሚክ ትምህርታቸው ጎን ለጎን አካላዊና ስነ-ልቦናዊ እድገታቸውን የሚያግዝ አስተማማኝ የመጫወቻ ስፍራ እንዲያገኙ ለማስቻል እንደሚረዳ ጠቁመዋል።
በቲካ የተደረገው ድጋፍ በኢትዮጵያ እና በቱርክ መካከል ያለውን ማህበራዊና ልማታዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ መሆኑ ገልፀው ለፕሮጀክቱ አስፈላጊውን የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ከፋውንዴሽኑ ጋር በጋራ በመስራቱ
አመስግነው የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት በሚቀይሩ መሠል ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፉ አመስግነዋል። በቲካ (TİKA) እና በደቦራ ፋውንዴሽን ትብብር የተከናወነው ይህ ፕሮጀክት በተለይ የዳውን ሲንድሮም እና ሌሎች የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህጻናት የሚያገለግል ነው ።
